የዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ አበባን የኮንፈረንስና የስበት ማዕከል እያደረጋት ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን በማስተናገድ አዲስ አበባን የኮንፈረንስና የስበት ማዕከል እያደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕከት÷ በኢትዮጵያ፣ አፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢንዱስትሪ ልማት (ዩኒዶ) በትብብር የተዘጋጀው ከረሃብ ነፃ ዓለም ጉባኤ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዶ ተጠናቅቋል።
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከተመረቀ ዕለት ጀምሮ የዚህ አይነት ታላላቅ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፈረንሶችን በማስተናገድ ከተማችንን የኮንፈረንስና የስበት ማዕከል እያደረጋት ይገኛል ብለዋል።
አዲስ አበባን የቱሪዝም፣ የኮንፈረንስ እንዲሁም የስበት ማዕከል ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት ታላላቅ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኮንፈረንሶችን ማስተናገድ መቻሉን ገልጸዋል።
ኮንፈረንሶች በአዲስ አበባ እንዲካሄዱ ትብብር ላደረጉ አካላትም ከንቲባ አዳነች ምስጋና ማቅረባቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡