Fana: At a Speed of Life!

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የቻይና ባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዱስትሪ ፓርኮች የቻይና ባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከቻይና-አፍሪካ ንግድ ምክር ቤት የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ተወያይቷል።

 

በውይይቱ የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ እንደገለፁት÷ የቻይና ባለሀብቶችን ለመሳብ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው፡፡

በተለይም ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቤጂንግ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና አዲስ አበባ ከሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ጋር በመተባበር የቻይና ባለሀብቶችን ለመሳብ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው 12 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና እና የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጣና ባለሀብቶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ገልጸው፤ የቻይና-አፍሪካ ንግድ ምክር ቤት አባላት ዕድሉን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የቻይና-አፍሪካ የልዑካን ቡድኑ መሪ ጆን ጂልስ (ዶ/ር)÷ ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዕድሎች በሰፊው የሚገኙባት ሀገር መሆኗን ገልፀው፤ ይህን የኢንቨስትመንት ትስስርን የበለጠ ለማጠናከር መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ይህንን እውነታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በመጪው መጋቢት ከ300 በላይ ከአፍሪካ እና እስያ የተውጣጡ ባለሀብቶች የሚሳተፉበት የኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ማመላከታቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.