Fana: At a Speed of Life!

አዘርባጃን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በይበልጥ ማሳደግ እንደምትፈልግ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አዘርባጃን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት በተለይም በኢኮኖሚያዊ አጋርነት እና ትብብር ለማስፋት ፍላጎት እንዳላት ተገለጸ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ሩስላን ናሲቦቭ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም አምባሳደር ናሲቦቭ አዘርባጃን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት በተለይም በኢኮኖሚያዊ አጋርነት እና ትብብር ለማስፋት ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል፡፡

በቅርቡም በሀገራቱ መካከል የተደረገውን የአየር አገልግሎት ስምምነት በአቪዬሽን ዘርፍ ትብብርን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በኮፕ 29 ጉባዔ ላይ እንድትሳተፍ አዘርባጃን ላቀረበችው ግብዣ ማመስገናቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ያለውን ምቹ የንግድ እና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በማብራራት÷ በቅርቡ በተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እየተፈጠሩ ባሉ በርካታ ጠቃሚ ዕድሎች የአዘርባጃን ባለሃብቶች ተጠቃሚ ለመሆን በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.