የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የሕዳሴ ግድብን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎበኙ።
በጉብኝቱ ላይ የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋን (ዶ/ር ኢ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እና የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክፍሌ ሆሮ (ኢ/ር) ለአምባሳደሮቹ ገለፃ አድርገዋል።
በወንድሙ አዱኛ