Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ወደ 75 በመቶ ማደጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ባለፈው በጀት ዓመት የ73 በመቶ የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ወደ 75 በመቶ ማሳደጉን የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ጥላሁን ሽመልስ÷ በ2016 በጀት ዓመት 900 የሚሆኑ የውሀ ተቋማት ተገንብተው ከ450 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በዚህም የክልሉን የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ወደ 75 በመቶ ማሳደግ መቻሉን በመግለጽ ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ የተበላሹ የውሃ ተቋማትን ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል።

በውሃው ዘርፍ አጋር አካላት ተሳትፏቸው ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሰው÷ በ2017 በጀት አመትም በወረዳ ደረጃ 800 ያህል የውሀ ተቋማት እንደሚገነቡ አመልክተዋል።

በዚህም ይንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋኑን ወደ 78 ለማድረስ ጥረት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

በስንታየሁ አራጌ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.