Fana: At a Speed of Life!

5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ማጠቃለያ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ማጠቃለያ መርሐ-ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር እየተካሄደ ነው ፡፡

መርሐ ግብሩ “የቁልፍ መሰረተ ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በዚህ ወቅት÷ የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ “በዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል መታወቂያ ሚና” በሚል ሃሳብ ውይይት እንደሚደረግ የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.