በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አርሰናል ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አቅንቶ ኒውካስል ዩናይትድን የሚገጥምበት ተጠባቂ ጨዋታ ቀን 9:30 ይደረጋል።
ምሽት 12:00 ላይ የሊጉ መሪ ማንቸስተር ሲቲ ከሜዳው ውጭ በርንማውዝን የሚገጥም ሲሆን÷ በተመሳሳይ ሰዓት ሊቨርፑል በአንፊልድ ብራይተንን ያስተናግዳል።
ኢፕስዊች ታውን ከሌስተር፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከዌስትሃም፣ ሳውዛምፕተን ከኤቨርተን በተመሳሳይ 12 ሰዓት የሚጫወቱ ሲሆን፥ ምሽት 2:30 ዎልቭስ ከክሪስታል ፓላስ የሚገናኙ ይሆናል።