Fana: At a Speed of Life!

አቶ እንዳሻው ጣሰው የተለያየ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የሕክምና ማዕከልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው በቡታጅራ ከተማ የተለያየ የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን ግራር ቤት ተሀድሶ ማዕከል ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸውም የማዕከሉን የሥራ እንቅስቃሴ፣ በማዕከሉ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን እና በሕክምና ላይ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተመልክተዋል፡፡

በማዕከሉ የአጥንት እና የጅማት ቀዶ ሕክምና ፣ የሚጥል በሽታ፣ የአካል ጉዳተኞች ሕክምናና ተሀድሶ፣ ከአንገት በላይ ሕክምናን ጨምሮ ሌሎች ተዛማጅ አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ የአካል ድጋፍ እና የመነጽር ማምረት ሥራ በማዕከሉ እንደሚከናወን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.