ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዛሬ ጠዋት መልዕክት ይዘው የመጡትን የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ልዩ መልዕክተኛ ዶክተር ማርቲን ኤልያ ሌሙሮን ተቀብያለሁ ብለዋል።
ባደረጉት ውይይትም በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ነው ያስታወቁት፡፡