Fana: At a Speed of Life!

ከ700 በሚልቁ ሕገ-ወጥ የንግድ ተቋማት ላይ ርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ700 በሚልቁ ሕገ-ወጥ የንግድ ተቋማት ላይ ርምጃ መወሰዱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዳንኤል ዳምጠው አስታወቁ፡፡

በቢሮው የኢንስፔክሽን ቡድን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በንግድ እንቅስቃሴው ላይ ክትትል እያደረገ መሆኑንም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ባለፉት አምስት ቀናት በ2 ሺህ 600 የንግድ ድርጅቶች ላይ በተደረገ ምልከታ÷ ከ700 በላይ የንግድ ድርጅቶች ያለ ንግድ ፈቃድ በመነገድ፣ ከዘርፍ ውጪ በመሥራት፣ ካስመዘገቡት ካፒታል በላይ ዕቃ በመያዝ ሲሠሩ ተገኝተው ሕጋዊና አሥተዳደራዊ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ብለዋል፡፡

ከተጣለባቸው አሥተዳደራዊ ቅጣትም እስከ አሁን 1 ሚሊየን 520 ሺህ ብር ለመንግሥት ገቢ ተደርጓል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

በንግድ ድርጅቶቹ ላይ በተደረገ ፍተሻ የሰዎችን ጤና የሚጎዱ ጊዜ ያለፈባቸው የምግብ ምርቶች፣ የለስላሳ መጠጦች፣ የቅባት ምርቶች መገኘታቸውን እና ከገበያ እንዲወገዱ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.