የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ ተሳታፊዎች የጤና ተቋማትን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ26ኛው ሀገር አቀፍ የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ ተሳታፊዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ወረዳዎችና ከተሞች የሚገኙ የጤና ተቋማትን እየጎበኙ ነው፡፡
በጉብኝታቸውም በተለያዩ የጤና ተቋማት ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የሕክምና ግብዓት እና የመሳሰሉ አሠራሮችን ተመልክተዋል፡፡
በጉብኝቶቹ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የጤናው ዘርፍ አመራሮች የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
26ኛው ሀገር አቀፍ የጤና ዘርፍ ጉባዔ ነገ በአርባ ምንጭ ከተማ እንደሚጀመርም ተገልጿል፡፡
በሳሙኤል ወርቃየሁ