የእንስሳት ዘርፍ ዐውደ-ርዕይ እና ጉባዔ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ትኩረቱን የእንስሳት ሃብት ልማት እና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች ላይ ያደረገ የእንስሳት ዘርፍ ዐውደ-ርዕይ እና ጉባዔ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ፡፡
ለሦስት ቀናት በሚቆየው ዐውደ-ርዕይ ላይም ከሀገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት በተጨማሪ የዘርፉ ባለሙያዎች እና አብረው መሥራት የሚፈልጉ ነጋዴዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ከ14 ሀገራት የተውጣጡ ከ100 በላይ ዓለም አቀፍ የእንስሳት ሃብት ዘርፍ ተዋናዮች እንደሚሳተፉ መገለጹን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
በአጠቃላይ ጉባዔው የእሴት ሰንሰለቱን የሚወክሉ መሰረታቸውን ከተለያዩ ሀገራት ጋር ካደረጉ የዘርፉ ኩባንያዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር እንደሚስችልም ነው የተገለጸው፡፡
ከ5 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ፣ የምሥራቅ አፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ሀገራት ጎብኚዎችም ጉባዔውን እንደሚመለከቱት ይጠበቃል ተብሏል፡፡