የዋጋ ግሽበት ወደ 17 በመቶ ዝቅ ብሏል- ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገሪቱ የነበረው የዋጋ ግሽበት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 26 በመቶ ወደ 17 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብስባ እየተካሄደ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት የዋጋ ግሽበት ዓለም አቀፍ ፈተና መሆኑን ገልጸው÷ ኢትዮጵያም የዋጋ ግሽበትን ለመቅረፍ በርካታ ስራዎችን እያከናወነች መሆኗን አስታውቀዋል፡፡
በዚሁ መሠረት በዋናነት እንደመፍትሔ የተያዘው ምርትን ማብዛትና የንግድ ሥርዓትን ማዘመን ነው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም መንግስት የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል በርካታ የድጎማ ስራዎች እያከናዎነ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
ለአብነትም ባለፉት ሦስት ወራት ለነዳጅ ዘርፍ 35 ነጥብ 7 ቢሊየን ፣ በበጀት ዓመቱ ለሴፍቲኔት 80 ቢሊየን፣ ለዘይት 9 ቢሊየን እንዲሁም ለማዳበሪያ 53 ቢሊየን ብር ለድጎማ መመደቡን አብራርተዋል፡፡
በዚህም ባለፈው ዓመት 26 በመቶ የነበረው የዋጋ ግሽበት ዘንድሮው ወደ 17 በመቶ ዝቅ ማለቱን አንስተዋል፡፡
በአመለወርቅ ደምሰው