Fana: At a Speed of Life!

ከመገናኛ ዐደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ በሁለቱም አቅጣጫ ለተሽከርካሪ ዝግ ሆኗል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመገናኛ ዐደባባይ ወደ ቦሌ እና ከቦሌ ወደ መገናኛ ዐደባባይ ያለው መንገድ በሁለቱም አቅጣጫ ላልተወሰነ ጊዜ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

በመገናኛ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት የሚያግዝ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላላፊያ መስመር ግንባታ መጀመሩንም ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው፡፡

ለዚሁ ሥራ ሲባልም ከመገናኛ ዐደባባይ ወደ ቦሌ እና ከቦሌ ወደ መገናኛ ዐደባባይ ያለው መንገድ በሁለቱም አቅጣጫ ለተሽከርካሪ ዝግ ሆኗል ብሏል::

እግረኞችም መገናኛ በሚገኘው ሙሉጌታ ዘለቀ ሕንጻ በኩል ማለፍ እንደማይቻል አውቀው በቦሌ ክፍለ ከተማ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት ባለው የእግረኛ መንገድ እንዲጓዙ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

አሽከርካሪዎችም ሌሎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንደሚጠበቅባቸው ነው ባለስልጣኑ ያሳወቀው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.