Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ 10 ሺህ ወታደሮች ለሩሲያ ወግነው እንዲዋጉ መላኳን አሜሪካ አስታወቀች

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ 10 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮች በሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት ሩሲያን ወግነው እንዲዋጉ መላኳን የአሜሪካ መከላከያ መስሪያ ቤት (ፔንታገን) አስታውቋል፡፡

የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች አሁን ላይ በምስራቅ ሩሲያ እንደሰፈሩ የተገለጸ ሲሆን÷ በቀጣይ ሳምንታት ስልጠና በመውሰድ ሩሲያን ወግነው ዩክሬንን ይዋጋሉ ተብሏል፡፡

ፔንታገን ፒዮንግያንግ ለሩሲያ ወታደሮችን በመላክ በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት መሳተፏ ችግሩን ይበልጥ ሊያበብሰው እንደሚችል አመልክቷል፡፡

የፔንታገን ቃል አቀባይ ሳብሪና ሲንግ 10 ሺህ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ለወታደራዊ ስልጠና ምስራቅ ሩሲያ መድረሳቸውንና 3 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ወደ ዩክሬን ድንበር መጠጋታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ዩን ሱክ ዮል በበኩላቸው÷የሰሜን ኮሪያ ወታደሮቿን ወደ ሩሲያ መላክ ለደቡብ ኮሪያም ሆነ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የደህንነት ስጋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሁለቱ ሀጋራት መካከል የተፈጠረው ወታደራዊ ትብብር ሕገ-ወጥ ድርጊት ነው ሲሉ መኮነናቸውንም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) ዋና ጸሃፊ ማርክ ሩት÷ የሰሜን ኮሪያ ድርጊት የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እየተባባሰ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በተያዘው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚመክሩም በዘገባው ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.