Fana: At a Speed of Life!

 ኢትዮጵያና ኡጋንዳ ነባሩን የአየር አገልግሎት ለማሻሻል ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ኡጋንዳ ነባሩን የአየር አገልግሎት ለማሻሻል መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያና ኡጋንዳ መካከል ቀደም ሲል ሲሰራበት የነበረውን የአየር አገልግሎት ስምምነት በያማምስኩሩ ስምምነት መሠረት እንዲሻሻል ኢትዮጵያ  ጥያቄ ማቅረቧተመላክቷል፡፡

ጥያቄውን ተከትሎም የሁለቱ ሀገራት ሲቪል አቪዬሽን ሃላፊዎች ተወያይተው የያማምስኩሩ ስምምነት እንዲከናወን   ተስማምተው ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያለምንም የምልልስና የመዳረሻ ቦታዎች ገደብ ወደ ኡጋንዳና ከኡጋንዳ ወደሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በረራ ማድረግ ያስችለዋል ተብሏል።

ስምምነቱ ከጥቂት ቀናት በፊት በማሌዢያ ኩዋላላምፑር ከተማ በተካሄደው የአየር ስምምነት መድረክ ላይ መፈረሙ ነው የተገለጸው፡፡

የያማምስኩር ስምምነት በፈረንጆቹ 1999 በኮትዲቯር ያማምስኩሩ ከተማ የአፍሪካ ሀገራት በአፍሪካ ምድር ለሚሰጡት የአየር ትራንስፖርት ነጻ የአየር አገልግሎት እንዲያገኙ የተፈረመ ስምምነት ነው፡፡

በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን 3 ጊዜ በሳምንት ደግሞ 21 ጊዜ ወደ ኡጋንዳ መዲና ኢተንቤ በረራ እንደሚያደርግ የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.