Fana: At a Speed of Life!

የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ተግዳሮት ለመፍታት  እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአምራች ኢንዱስትሪ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እየተሠራ መሆኑን የብሔራዊ አምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል ሰብሳቢና የጠቅላይ ሚኒስትር የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ ገለጹ፡፡

ካውንስሉ በሰበታ እና አዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝቷል፡፡

በዚሁ ወቅትም ካውንስሉ ከፋብሪካዎች አሥተዳደር አባላት ጋር እስከ አሁን እያጋጠሙ ባሉ ተግዳሮቶችና በተገኙ አበረታች ለውጦች ላይ ምክክር አድርጓል፡፡

አምባሳደር ግርማ  በዚሁ ወቅት ÷ በየጊዜው የሚታዩትን የዘርፉን ማነቆዎች በአፋጣኝ ለመፍታት መንግስት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የካውንስሉ አባላትም የኤልኮ ቆዳ ፋብሪካን፣ የቡልኮንና የአልሳም ዲማ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል፡፡

አሠራራቸውን በተመለከተም ቀጣይነት ያለው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግላቸው መገለጹን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትና ምርታማነት  ለማሳደግ ብሎም ጥሩ የስራ አፈፃፀምና አርዓያነት ያላቸውን ኢንዱስትሪዎች ለመደገፍና ተሞክሯቸውን ወደ ሌሎች ለማስፋት አስቦ ካውንስሉን ማቋቋሙ ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.