Fana: At a Speed of Life!

 በአዋሽ ፈንታሌ የተለያየ ደረጃ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ ቀበሌ ጎምዲሊ በተባለ ሥፍራ እስከ 4 ነጥብ 7 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የተለያየ ደረጃ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ሠመራ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ ትናንት ከማለዳው 11 ሠዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 9 ሠዓት 21 ላይ ቢከሰትም ጉዳት አለመድረሱን በዩኒቨርሲቲው የሥነ-ምድር ጥናት መምህር ኖራ የኒሞኖ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ትናንት በተለያየ ሠዓት ከተከሰተው የመሬት መንቀጥ ቀን 9 ሠዓ 21 ላይ የተከሰተው ከፍ ያለ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የአካባቢዎች ነዋሪዎች በበኩላቸው ትናንት የተከሰተው ቀደም ሲል ከነበሩት ከፍተኛ መንቀጥቀጥ ነበረው ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመሬት መንቀጥ ቀጥ ወቅት መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች እና ሌሎችተያያዥ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.