Fana: At a Speed of Life!

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ለኢኮኖሚው አስተዋጽኦ እንዲያደርግ መሥራት ይገባል – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ያሉበትን ማነቆዎች በመፍታት ለኢኮኖሚው የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ አሳሰቡ።

አቶ አረጋ ከበደ፣ የክልሉ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሀመድ (ዶ/ር) እንዲሁም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ባለድርሻዎች በተገኙበት ክልላዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ እንዳሉት፤ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ያሉበትን ማነቆዎች በመፍታት ለኢኮኖሚው የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል።

በክልሉ የነበረው የፀጥታ ችግር የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው እንቅፋት መሆኑን ጠቅሰው፤ ችግሩ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት ማጠናቀቅ ያስቻለ የፕሮጀክት አስተዳደር ልምድ የማምጣት ጥረትን ማጓተቱን ተናግረዋል።

የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ አህመዲን አህመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በክልሉ 648 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች እንዳሉ ጠቅሰው፤ በተለያዩ ችግሮች በሚፈለገው ልክ ውጤታማ እንዳልሆኑ ገልጸዋል።

የምክክር መድረኩ ዘርፉ ያጋጠሙትን ፈተናዎች ለይቶ ቅንጅታዊ አሠራርን በማሳደግ በባለቤትነት ለመፍታትና ውጤታማ የፕሮጀክት አስተዳደርን እውን ለማድረግ ይረዳል ብለዋል።

በደሳለኝ ቢራራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.