Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የማሌዢያ የንግድ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት እድል እንዲጠቀሙ ጥሪ አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማሌዢያ የንግድ ማኅበረሰብ በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን የኢንቨስትመንት እድል እንዲጠቀሙ አበረታታለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

በማሌዢያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ብሎም የማሌዢያ ሕዝብ እና መንግሥት በቆይታችን ለሰጣችሁን ደማቅ አቀባበል እና ፍቅር እናመሰግናለን ብለዋል።

ትብብራችንን ትኩረታቸውን በግብርና፣ ማዕድን፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ታዳሽ ኃይል ላይ ባደረጉ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ብሎም ሰፊ አድማስ ባላቸው ሌሎች ቁልፍ ሥራዎች ላይ ለማጠናከር ተስማምተናል በማለትም ገልጸዋል።

የማሌዢያ የንግድ ማኅበረሰብ በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን የኢንቬስትመንት እድል እንዲጠቀሙ አበረታታለሁ በማለትም ጥሪ አስተላልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.