Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብሮች በዛሬው እለት ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡

ቀን 11 ሰዓት ላይ በሊጉ ሰንጠረዥ በ20 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ ሳውዝአምፕተንን ያስተናግዳል።

በተመሳሳይ ሰዓት አስቶንቪላ ከቦርንሞውዝ፣ ብሬንትፎርድ ከኢፕስዊች ታውን፣ ብራይተን ከዎልቭስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ምሽት 1 ከ30 ላይ ደግሞ በጉዲሰን ፓርክ ኤቨርተን ፉልሃምን ይገጥማል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሰኝጠረዥ የመርሲሳይዱ ሊቨርፑል በ21 ነጥብ ይመራል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.