ለአዲስ አበባ መንገዶች ጥገና የሚውል የ386 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ ታህሳስ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጃፓን ለአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ጥገና የሚውል የ386 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ማትሱናጋ ዳይሱኬ ተፈራርመውታል።
የድጋፍ ስምምነቱ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ መንገዶችን ለማሻሻል ለሚተገበረው ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል ነው ተብሏል።
መረጃው በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ ነው፤