የሞንጎሊያ ልዑክ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎበኘ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞንጎሊያ ሕዝቦች ሪፐብሊክ የፓርላማ አባልና የቀድሞ የአካባቢ ሚኒስትር ኡልዚ ባት-ኤርዴኔ የተመራ ልዑክ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝቷል።
ጉብኝቱ በኢትዮጵያ እና በሞንጎሊያ መካከል የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጎልበት እና በዘላቂ ልማት በተለይም በውሃ አያያዝ እና በአየር ንብረት ለውጥ መላመድ ላይ መልካም ተሞክሮዎችን መለዋወጥን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።
ልዑኩ ከውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)፣ ከፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስዩም መኮንን እና ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ነገዎ (ዶ/ር) ጋር መወያየቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡