Fana: At a Speed of Life!

ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ ወታደራዊ አታሼዎች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሠራዊት ቀንን በማስመልከት ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ ወታደራዊ አታሼዎች፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

የመከላከያ ውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ ÷ የሠራዊቱ የጀግንነት፣ ከአኩሪ ተጋድሎና ታላቅ የሃገር ፍቅር ስሜት ጋር የተላበሰ አኩሪ ገድሎችን በሚገባው ልክ ለመዘከር፣ የተቋሙን ቀጣይነት ያለው አቅም ግንባታ ስራን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማረጋገጥ ቀኑ እንደሚከበር ተናግረዋል፡፡

የሁለትዮሽና የሶስትዮሽ ትብብሮችን አጠናክሮ ከማስቀጠል አንፃር በድል ላይ በመሆን የሚከበር የሰራዊት ቀን የሚኖረውን በጎ ተፅዕኖ ከማስገንዘብና በተጨማሪ ሰራዊቱ በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ለአኩሪና ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን ለህዝብ፣ ለወዳጆችና ለጠላትደግሞ በሚገባ ለማስገንዘብ መሆኑን አሥረድተዋል፡፡

የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች የበዓሉ ተካፋይ በመሆናቸው እንደሠታለን ያሉት ሜጄር ጄኔራል ተሾመ ÷ ሰፊውን የኢትዮጵያን ሠራዊት ታሪክና በዓለማቀፍ በአህጉራዊና በቀጠናው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ያበረከተውን ታላቅ አስተዋጽኦ ዓለም ሁሌም የማይዘነጋው ነው ብለዋል፡፡

ለ117ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በዓልም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የመድረኩ ተካፋይ የሆኑ ወታደራዊ አታሼዎች፣ አህጉራዊ ድርጅቶችና የዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች በነበራቸው ቆይታ ደስተኛ መሆናቸውንና ጥሩ ልምድ ማካበታቸውንም ገልጸዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.