የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት 3 ቀናት ወደ ሞንሮቪያ ለመብረር መዘጋጀቱን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሕዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት ሦስት ቀናት ወደ ላይቤሪያ ሞንሮቪያ የሚያደርገውን የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ ወደ ሞንሮቪያ በሣምንት ሦስት ቀናት መብረሩ በምዕራብ አፍሪካ ያለውን ግንኙነት እንደሚያጎለብተው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በምዕራብ አፍሪካ እና ለአካባቢው ኢኮኖሚ እድገት ከፍኛ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት መገለጹን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡