Fana: At a Speed of Life!

8ኛው የአፍሪካ ሕብረትና የተመድ ከፍተኛ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 8ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የትብብር ምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝን ጨምሮ የተቋማቱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ የአፍሪካ ሕብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትብብር ማዕቀፎች አፈጻጸም እንደሚገመገም ተመላክቷል፡፡

ሁለቱ ተቋማት ሰላም እና ደህንነትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸው ትብብር ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.