Fana: At a Speed of Life!

ማቼስተር ሲቲ ዎልቭስን 2 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ8ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ሞሊኒክስ ስታዲየም አቅንቶ ከዎልቭስ ጋር ጨዋታውን ያደረገው ማንቼስተር ሲቲ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

በጨዋታው ዎልቭስን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ ኖርዌጂያኑ ስትራንድ ላርሰን ሲያስቆጥር÷ የውኃ ሰማያዊዮቹን ግቦች ክሮሽያዊው ጆስኮ ግቫርዲዮል እና ጆን ስቶንስ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ የዛሬ መርሐ-ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ከ30 ላይ ሊቨርፑል ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.