Fana: At a Speed of Life!

በሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳዎችን በመለየት ረገድ ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራዊ ምክክሩ ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን አጀንዳዎች በመለየት ረገድ ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የባለድርሻ አካላት አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር መድረክ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

መስፍን አርአያ(ፕ/ር)  በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኮሚሽኑ እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ያለመግባባቶችን ለይቶ በምክክር መፍትሄ ለማምጣት ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

ኢትዮጵያ ዘመን የተሻገሩ ችግሮች ወጥረዋት በርካታ ኪሳራዎችን እያስተናገደች እዚህ መድረሷንም አስረድተዋል፡፡

ከመቅረት መዘግየት እንዲሉ.. እንደ ሀገር አሁን ላይ ይህን ዘመን ተሻጋሪ ችግር ከስሩ ገርስሰን ለመንቀል በጋራ ተነስተን እየመከርን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የሶማሌ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው አጀንዳዎች የሚለዩበት እንደሚሆን እምነታቸው መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.