Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል መሆኗ ተገለጸ።

በጄኔቫ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጸጋአብ ክበበው ደግሞ በኮሜቴው የአፍሪካን ቡድን በመወክል ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ነው የተገለፀው፡፡

አምባሳደር ጸጋአብ በመንግሰታቱ ድርጅት የተካሄዱ የባለብዙ ወገን መድረኮችን በመምራት እንዲሁም በጄኔቫ በጤና ጉዳዮች ላይ የአፍሪካ አምባሳደሮች ቡድን አስተባባሪ በመሆን ልምድ አካብተዋል።

በመሆኑም ባካበቷቸው ተሞክሮዎች ምክንያት በምክትል ሊቀመንበርነት መመረጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.