Fana: At a Speed of Life!

በጫሞ ሐይቅ ላይ የደረሰውን የጀልባ መስጠም አደጋ ተከትሎ የነፍስ አድን ሥራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአቡሎ አርፋጮ ወደ አርባምንጭ ከተማ 16 ሰዎችን እና ሙዝ ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ጫሞ ሐይቅ ላይ መስጠሟን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜም ሶስት ሰዎች በሕይወት መገኘታቸውን መምሪያው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጧል፡፡

አደጋው ትናንት 10 ሠዓት ከ20 ገደማ መከሰቱን የገለጹት በመምሪያው የሕዝብ ግንኙነትና ገጽታ ግንባታ ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ÷ አሁንም የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ ከልክ በላይ መጫን ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቁመው÷ በጀልባዋ ላይ የነበሩት ተሳፋሪዎች የቀን ሠራተኞች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.