Fana: At a Speed of Life!

በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው በ13 መዝገብ የተከሰሱ ግለሰቦች ከአንድ ዓመት እስከ 25 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ፡፡

በዚህም በ13 የክስ መዝገብ ተከሰው የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባቸው፡-

1ኛ. ተካ ወ/ማርያም በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እና 28 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፤ በሌላ የክስ መዝገብ ደግሞ 16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት፣

2ኛ. ለማ ተማሮ 10 ዓመት ጽኑ እስራት፣

3ኛ. መለሰ ካህሳይ 11 ዓመት ጽኑ እስራትና 76 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

4ኛ. ደመቀች ማጉጂ 15 ዓመት እስራት እና 30 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

5ኛ. ስምኦን ተወልደ 3 ዓመት ከ7 ወር እስራት እና 4 ሺህ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት ፣

6ኛ. ዮሃንስ ፍስሃዩ 5 ዓመት ከ7 ወር እስራትና 7 ሺህ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት፣

7ኛ. ሀና ዲኖ 3 ዓመት ከ3 ወር እስራትና 2 ሺህ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት፣

8ኛ. ረዳት ሳጅን መሀመድ አህመድ 6 ዓመት እና 8 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

9ኛ. ገ/ትንሳኤ ሀጎስ በ16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና 80 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

10ኛ. አብዱል ሽኩር ይማም 10 ዓመት እና 11 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

11ኛ. ሙህዲን አማን መሀመድ 10 ዓመት እና 11 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

12ኛ. አብዱላዚዝ ራህመቶ ዳንቴቦ 5 ዓመት እና 6 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

13ኛ. ዘላለም ብርሃኑ 5 ዓመት እስራት እና 3 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

14ኛ. ናርዶስ ሀብቴ ደበሌ 4 ዓመት ከ5 ወር እስራት እና 3 ሺህ 500 ብር የገንበዘብ ቅጣት፣

15ኛ. ፍሬሕይወት በላይ ግርማ 6 ዓመት እስራት እና 110 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

16ኛ. ቅዱስ ኃ/ሚካኤል ሳምቢ 4 ዓመት ከ5 ወር እስራት እና 3500 ብር የገንዘብ ቅጣት፣

17ኛ. ሚኪያስ ተሾመ ፈጡላ 410 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በ13 የምርመራ መዝገቦች ሲታይ የቆየውን የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የወንጀል መዝገብ መርምሮ ከአንድ ዓመት እስከ 25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲሁም ከ2 ሺህ ብር እስከ 410 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ወስኖባቸዋል።

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.