የአፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮች የደህንነት ተቋማትን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች እና ወታደራዊ አታሼዎች የኢትዮጵያ የደህንነት ተቋማትን እየጎበኙ ነው።
ኢትዮጵያ እያስተናገደች ባለው የአፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ እንግዶች በተለያዩ ተቋማት ጉብኝት እያካሄዱ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎብኝተዋል።
በሌሎች ተቋማትም ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮችና ወታደራዊ አታሼዎቹ በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ አየር ሃይልን እና የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪን መጎብኘታቸው ይታወሳል።
በሳሙኤል ወርቃየሁ