Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ለሽያጭ ዝግጁ መሆን የታሪካዊ ክንውን ምዕራፍ ማሳያ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ የአክሲዮን ለሽያጭ ይፋ አድርገዋል፡፡

ይህን ተከትሎም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በዛሬው ዕለት 10 በመቶ የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ለሽያጭ ዝግጁ መሆኑ የታሪካዊ ክንውን ምዕራፍ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ባለፉት ስድስት ዓመታት ከፖለቲካዊ አብዮት ወደ የለውጥ መንገድ እየተደረገ ያለው ስኬታማ ጉዞ ማሳያ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

እንደ ዲጂታል ኢትዮጵያ ያሉ ቁልፍ የለውጥ ሥራዎች መተግበራቸውም ለዛሬው ታሪካዊ ሁነት ፅኑ መደላድል ፈጥረዋል፤ በተለያዩ ዘርፎችም የሚታይ እድገትን አስችለዋል ነው ያሉት።

50 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን የገንዘብ ዝውውር ተግባራቸውን በሞባይል እንደማከናወናቸውም የ130 ዓመታት ዕድሜ ባለፀጋው ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻውን በሽያጭ ለሕዝብ አቅርቧል ነው ያሉት፡፡

ይህ ለኢትዮጵያ የአክሲዮን ገበያ መደላድል የሚፈጥር ብሎም በሀገራችን ካሉ ቀዳሚ መንግሥታዊ የንግድ ተቋማት (አሁን ወደ አክሲዮን ድርጅትነት የተለወጠ) አንዱ ከሆነው ከአንጋፋው ኢትዮ ቴሌኮም የባለቤትነት እድልን የሚያሰፋ ክንዋኔ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.