Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሐረሪ ክልል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ትምህርት ቤቶችና ባለድርሻ አካላት እውቅና እና ማበረታቻ ተሰጠ፡፡
በክልሉ የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 2 ሺህ 525 ተማሪዎች÷ 13 ነጥብ 3 በመቶ ያህሉ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመግባት የሚያስችል ነጥብ ማስመዝገባቸው ተገልጿል፡፡
በ2016 ዓ.ም የተመዘገበው ውጤት አበረታች መሆኑን የገለጹት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ነገዎ÷ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎችን ውጤትን በይበልጥ ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራት ላይ በትኩረት ይሠራል ብለዋል፡፡
በክልሉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያስፈተኑ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የተለያየ ቁጥር ያለው ተማሪ ማሳለፍ መቻላቸውንም ገልጸዋል፡፡
በቲያ ኑሬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.