Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ የሱዳን የወደብ ከተማ ወደሆነችው ፖርት ሱዳን የሚያደርገውን ዕለታዊ በረራ ጀምሯል፡፡

ፖርት ሱዳንን 66ኛ የአፍሪካ መዳረሻው ያደረገው አየር መንገዱ ወደ ፖርት ሱዳን በረራ መጀመሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሀገራት ያላትን የመዳረሻ ቁጥር የበለጠ እንደሚያሰፋው ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው÷ሃገራትን ከአፍሪካ እና ከመላው ዓለም የማገናኘት ስራ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

በቴክኖሎጂ የበለፀጉ አዳዲስ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ለደንበኞች የአገልግሎት ደረጃ እያሳደግን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ሁሉም የአየር መንገዱ አገልግሎቶች ቱሪዝምን፣ ንግድን፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ላይቤሪያ መዲና ሞንሮቪያ በረራ እንደሚጀምርም ተገልጿል።

በትዕግስት አስማማው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.