Fana: At a Speed of Life!

የባሕር በር በሊዝ እስከ መስጠት የደረሰ መልካም ጉርብትና…

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ በደቡባዊ ምሥራቅ የአፍሪካ ክፍል የምትገኘው ሞዛምቢክ የባህር በር ለሌላት ጎረቤቷ ማላዊ የባሕር በር በሊዝ ሰጥታለች።

ከማላዊ ጋር ረጅም ድንበር የምትጋራት ጎረቤቷ ሞዛምቢክ በአንፃሩ በምሥራቃዊ ክፍሏ በረዥሙ ከህንድ ውቅያኖስ ጋር የምትዋሰን ሀገር በመሆኗ የማላዊን የባህር በር ችግር ለመፍታት ቅንነት የተሞላበት ውሳኔ አሳልፋለች።

በዚህ ውሳኔዋም ወደብ አልባዋ ጎረቤቷ ማላዊ በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ከሚገኙ የማላዊ ወደቦች መካከል አንዱ በሆነው ናካላ የራሷን መሠረተልማቶች ገንብታ እንድትጠቀም መፍቀዷ ነው የተሰማው።

ማላዊም ከዋና ከተማዋ ሊሎንግዌ ተነስቶ በሞዛምቢክ ሉዓላዊ ግዛት እስከህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ የሚያደርሳትን ናካላ ኮሪደር ልማት እያከናወነች ሲሆን፤ ገቢና ወጪ ንግዷን ራሷ በምታለማው የናካላ ወደብ በኩል ታከናውናለች።

ሁለቱ ጎረቤታሞች በጋራ መልማቱ ይበልጥ የተሻለው አማራጭ ነው ብለው በተለያዩ መስኮች ትብብራቸውን በማጠናከርም ላይ ናቸው።

ከሊሎንግዌና ማፑቶ እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እንዳመላከቱት፤ ጎረቤታሞቹ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትና የአየር ትራንስፖርትን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.