የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ ይከበራል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ በመላ ሀገሪቱ ተከብሮ ይውላል፡፡
የሰንደቅ ዓላማ ቀን የጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡
17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ሀገራዊ ይዘት ባላቸው የተለያዩ መልዕክቶች ይከበራል፡፡
ከመልዕክቶቹ መካከልም÷ ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን፣ ሰንደቅ ዓላማችን የኅብረ-ብሔራዊነታችን ማሳያ፤ የአንድነታችን የጋራ ዓርማ፣ ሰንደቅ ዓላማችን የኅብረ-ብሔራዊ አብሮነታችን ዋስትና ነው እና ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነታችን መገለጫ ነው የሚሉት ይገኙበታል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ምንም እንኳ ወቅታዊ ፈተና ቢያጋጥማትም አሸንፋ ትሻገራለች፣ በልጆቿ መስዋዕትነት የኢትዮጵያ አንድነት ፀንቶ ይቀጥላል፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን የሉዓላዊነታችን አርማ ነው እንዲሁም ሰንደቅ ዓላማችን ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ የሚሉት ከ17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን መልዕክቶች መካከል ይገኙበታል፡፡