Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ምርትን ለገበያ ለማቅረብ ሰፊ የገበያ ትስስር ስራ እናከናውናለን – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ምርትን ለገበያ ለማቅረብ ሰፊ የገበያ ትስስር ስራ እናከናውናለን ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደረ ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የሰንበት ገበያዎችንና የወርቅ ማውጫ ቦታዎችን ጎብኝተናል ብለዋል።

እንዲሁም የተለያዩ እምቅ የልማት አቅሞችን በአቦቦ ወረዳ ሉንጋ ቀበሌ እና አቦቦ ከተማ አስተዳደር ተገኝተን ጎብኝተናል ሲሉ ገልጸዋል።

በክልሉ ገና ያልተነካ የልማት አቅም አለው ያሉት ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፤ በክልሉ በስፋት ለማምረትና የተመረተውን ምርት ምርት ለገበያ ለማቅረብ ሰፊ የገበያ ትስስር ስራ የምናከናውን ይሆናል ብለዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.