Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ሞሮኮ ፖሊስ ተቋማት በጋራ መሥራት የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ከሞሮኮ የግዛት ቁጥጥር ዋና ዳይሬክተር ም/ ሃላፊና የሀገሪቱ ፖሊስ ኢንተለጀንስ ዳይሬክተር ፋራሀ ቦውልሃታህ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችንና ሽብርተኝነትን ለመከላከል እንዲሁም በሁለቱ የፖሊስ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ፋራሀ ቦውልሀታህ÷የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የደረሰበትን ሁሉን አቀፍ  የዘመነ የፖሊስ አገልግሎትና የታጠቃቸውን ቴክኖሎጂዎች አድንቀዋል፡፡

የኢትዮጵያና ሞሮኮ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ የተጠናከረ የረጅም ጊዜ ግንኙነት በፖሊስ ሥራዎችም ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.