Fana: At a Speed of Life!

ለአንስቴዥያ ሙያ ተመራቂዎች የተግባር የብቃት ምዘና ፈተና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንስቴዥያ ሙያ ተመራቂዎች የተግባር የብቃት ምዘና ፈተና በተመረጡ ስምንት ጣቢያዎች መሰጠቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ ዳግማዊ ሚኒልክ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ ጅማ፣ ድሬዳዋ፣ ሀዋሳ፣ አርሲ፣ ወሎ እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናው መሰጠቱ ተገልጿል።

የፈተናው ዋና ዓላማ የተመዛኞችን በተግባር የተደገፈ ክህሎት እና አመለካከት ለመለካት እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሯ፤ ፈተናው ከዚህ በፊት የተሰጠውን የጽሁፍ ፈተና ላለፉ 240 የአንስቴዥያ ተመራቂዎች እንደሆነ አመልክተዋል።

የተግባር ፈተና መሰጠቱ ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት በዕውቀትና ክህሎት የዳበረ የጤና ባለሙያ ቅድሚያ እንዲሰጥ የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።

ከዚህ በተጨማሪም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተግባር የተደገፈ ትምህርት እንዲሰጡ አስተዋፆኦ እንዳለው ተጠቁሟል።

በቀጣይም በጤናው ዘርፍ ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለማምጣት መሰል ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባወጡት መረጃ ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.