Fana: At a Speed of Life!

በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የፈለቀውን ውኃ ሕብረተሰቡ ለጊዜው እንዳይጠቀም ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የፈለቀው ውኃ አጠቃላይ ሁኔታ በጥናት እስከሚረጋገጥ ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀም ሠመራ ዩኒቨርሲቲ አሳሰበ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሥነ-ምድር ትምህርት ክፍል ዲን ሕንዳያ ገብሩ (ዶ/ር)÷ የፈለቀው ውኃ ምንነት፣ ይዘት፣ ጥቅምና ጉዳት በምርምር እስከሚረጋገጥ ሕብረተሰቡ ለማንኛውም አገልግሎት ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳስበዋል፡፡

የሥነ-ምድር ትምህርት ክፍል ኃላፊ ጌታቸው ገብረፃድቃን በበኩላቸው እስከ 1 ነጥብ 5 ሜትር የመሬት መሰንጠቅ መከሰቱን አስታውሰው÷ በስፍራው ያሉ ሰዎችን ወደ ሌላ ቦታ ማዛወር እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል፡፡

የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎችን በተከታታይ መሥራት እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.