Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልዑክ በሞሮኮ የልምድ ልውውጥ እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላምና ፀጥታ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፌዴራልና የክልል የጸጥታ ኃላፊዎችን ጨምሮ የሐይማኖት አባቶችን ያካተተ የኢትዮጵያ ልዑክ በሞሮኮ የልምድ ልውውጥ እያደረገ ነው፡፡

የልምድ ልውውጡ በሁለቱ ሀገራት ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው መገለጹን ሰላም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ሞሮኮ የተለያዩ ሐይማኖቶችና ሕዝቦች ተከባብረው እንዲኖሩ በማድረግ በአፍሪካ ጠንካራ ኢኮኖሚ የገነባችበት መንገድ ለኢትዮጵያ ጥሩ ልምድ እንደሚሆንም ነው የተገለጸው፡፡

ልዑኩ ራባት እና ካዛብላንካን ጨምሮ በአራት ትላልቅ ከተሞች ላይ የሚገኙ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ሐይማኖታዊ ተቋማትን እንደሚጎበኝም ተመላክቷል፡፡

ከተቋማቱ ኃላፊዎች ጋርም የሁለትዮሽ ግንኙነትን በይበልጥ ከማሳደግ አንጻር ምክክር እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.