Fana: At a Speed of Life!

አልጀሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አልጀሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ እና ዘርፈብዙ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች፡፡

በአልጄሪያ የኢትጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ሙክታር መሃመድ ዋሬ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱልመጂድ ተቡኔ አቅርበዋል።

አምባሳደር ሙክታር ከፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከ ልባዊ ሰላምታ እና የወዳጅነት መልዕክት ለፕሬዚዳንት ተቡኔ አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንት አብዱልመጂድ ተቡኔ÷አልጀሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊና ዘርፈብዙ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል ።

አምባሳደር ሙክታር በበኩላቸው÷ኢትዮጵያና አልጄሪያ ታሪካዊ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን እንዳነሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል፡፡

ሀገራቱ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ከፍተኛ ትግል በማድረግ ድርጅቱን እንዲጠናከርና የፖን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ እንዲጎለብት ያደረጉትን ጥረትም አስረድተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.