Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ21 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 በጀት ዓመት በተለያዩ መስኮች ከ21 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንት ታዬ ለሁለቱ የፌዴራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌዴራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ አቅርበዋል፡፡

በንግግራቸውም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 18 ነጥብ ዝቅ ማለቱን አንስተዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት የወጪ ንግድ ምርቶች ስብጥር እና አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎችን በማስፋት ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር መገኘቱንም ገልጸዋል፡፡

ይህም ከ2015 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ4 ነጥብ 8 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው ያስረዱት፡፡

በበጀት ዓመቱ ከሸቀጦች የወጪ ንግድ፣ ከአገልግሎት ዘርፍ፣ ከሃዋላ እና ከቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በአጠቃላይ ከ21 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ መገኘቱንም ተናግረዋል፡፡

በአቤል ንዋይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.