Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ሁለተኛው ምዕራፍ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ሁለተኛ ምዕራፍ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ የ5 ዓመት ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ላለፉት አምስት ዓመታት ሲተገበር ቆይቷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ÷ፕሮጀክቱ የክልሉ ሕዝብ ሕይወት እንዲቀየር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል።

በዚህም በቀጣይ በፕሮጀክቱ በምዕራፍ አንድ ተጀምረው በተለያዩ ምክንያቶች ያልተጠናቀቁትን ለማጠናቀቅ እና የፕሮጀክቱን ትግበራ በሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል፡፡

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ቢየል ቢቾክ(ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ሁለተኛው ዙር የመስኖና ቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በክልሉ በዘጠኝ ወረዳዎች በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት እንደሚተገበር ገልጸዋል።

በዚህ ምዕራፍ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን የጠቆሙት አስተባባሪው ÷ተቋማትና የሚመለከታቸው አካላት ለፕሮጀክቱ ተፈጻሚነት የድርሻቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.