Fana: At a Speed of Life!

ሆረ ፊንፊኔ ኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ደምቆ የታየበት ነው – ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የተከበረው ሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ደምቆ የታየበት ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ክብረ በዓሉን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከዋዜማ ጀምሮ የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ባማረ ድባብ፣ በከፍተኛ ድምቀትና ውበት ተከብሯል ብለዋል።

በዓሉ በእንግዳ ተቀባይነት ስሜት እሴት ስርዓቱን ጠብቆ በድምቀት ተከብሯል ሲሉም ገልጸዋል።

በዓሉ ኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ደምቆ የታየበት ከመሆኑም በላይ ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍ ያለ አስተዋጽ አለዉ ያሉት ሚኒስትሩ፤ መላው የመዲናዋ ነዋሪዎችና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላሳዩት ታላቅ የአብሮነትና የእንግዳ ተቀባይነት ስሜት ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.