Fana: At a Speed of Life!

ሊቨርፑል ከክሪስታል ፓላስ፣ አርሰናል ከሳውዝ ሃምተን፣ ማንቼስተር ሲቲ ከፉልሃም የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰባተኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በዚሁ መሠረት ክሪስታል ፓላስ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል ጋር 8 ሠዓት ከ30 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረት ስቧል፡፡

እንዲሁም 11 ሠዓት ላይ ከሊቨርፑል በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ በሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ ሁለተኛ ላይ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ከፉልሃም ጋር ይጫወታል፡፡

በሌላ በኩል በተመሳሳይ 11 ሠዓት ላይ ከውኃ ሰማያዊወቹ ጋር በነጥብ እኩል ሆኖ በጎል ክፍያ ተበልጦ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከሳውዝ ሃምተን ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

በተመሳሳይ 11 ሠዓት ላይ ብሬንትፎርድ ከዎልቭስ፣ ዌስትሃም ከኢፕስዊች ታውን እና ሌስተር ሲቲ ከቦርንማውዝ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ኤቨርተን ከኒውካስል ጋር ምሽት 1 ሠዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የወጣው መርሐ-ግብር ያስረዳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.