Fana: At a Speed of Life!

በግብርናው ዘርፍ ከ144 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ በግብርናው ዘርፍ ከ144 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በተገኙበት የ2017 ዓ.ም የበጋ የተቀናጀ ግብርና ልማት ንቅናቄ መድረክ ”የተቀናጀ ግብርና ለቤተሰብ ብልፅግና” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ነው፡፡

በበጋ የተቀናጀ ግብርና ልማቱ በምግብና ሥነ -ምግብ፣ በገቢ ንግድ፣ በወጪ ንግድ፣ በኢንዱስትሪ ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በቤተሰብ ምግብ ዋስትና ላይ ትኩረት እንደሚደረግ የቢሮው ኃላፊ ኡስማን ሱሩር አብራርተዋል፡፡

የተያዘው ዕቅድ እንዲሳካም የግብርና ቴክኖሎጂዎች ሥራ ላይ እንደሚውሉ ጠቅሰው÷ በበጀት ዓመቱ ከ144 ሺህ በላይ ዜጎች በዘርፉ የሥራ ዕድል እንዲያገኙ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

በቢቂላ ቱፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.