Fana: At a Speed of Life!

ከ4 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ ከቀረጥ ነጻ የመገበያያ ማዕከል ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ በ14 ሺህ 539 ካሬ መሬት ላይ ከቀረጥ ነጻ የመገበያያ ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እና የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ራሄል ጌታቸው ናቸው፡፡

ወ/ሮ ራሄል በዚሁ ወቅት ስምምነቱ የመጀመሪያ የሆነና ከቀረጥ ነጻ የመገበያያ ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ግንባታውም ከአየር መንገዱ ካርጎ አጠገብ በሚገኝ 14 ሺህ 539 ካሬ መሬት ላይ የሚያርፍና በ4 ነጥብ 3 ቢልየን ብር የሚከናወን ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አቶ መስፍን በበኩላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገሪቱ ቱሪዝም እንዲያድግ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰው÷ ስምምነቱ የቱሪዝም ዘርፉን በጋራ ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.