Fana: At a Speed of Life!

ትምህርት ቤት ከመገንባት ባለፈ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ መትጋት እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ቤቶችን ከማስፋፋት ባሻገር የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተስፋ ሰጪ ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ኢብራሂም ኡስማን አስገነዘቡ፡፡

ለሦስት ቀናት የሚቆየው 33ኛው የሶማሌ ክልል የትምህርት ጉባዔ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ ኢብራሂም በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ከለውጡ ወዲህ የክልሉ መንግሥት ኩረጃን ለማስወገድ፣ የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን በማሻሻል በኩል በርካታ ሥራዎችን አከናውኗል ብለዋል፡፡

ብቁ የተማረ ትውልድን ለማፍራት ተጨማሪ ትምህርት ቤቶችን ከመገንባትና ከማስፋፋት ባሻገር የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተስፋ ሰጪ ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴዔታ አየለች እሸቴ በበኩላቸው÷ የትምህርት ጥራትን በማሳደግ ብቁ የተማረ ትውልድን ለመፍጠርና የተጀመሩ ሥራዎችን ለማጠናከር በቅንጅት መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.